Addis Ababa City Food and Drug Authority Akaki Kality Sub-city Branch
Akaki Kality Administration Building

የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ

የምግብና ጤና-ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር

የምግብና ጤና-ነክ ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክተር

የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ብቃት ዳይሬክተር

የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር

የባለስልጣኑ ተልዕኮ ፤ራዕይና እሴቶች፤

ተልዕኮ

የምግብ ፤ጤና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ የምርትና አገልግሎት ደህንነትና ጥራት እንዲረጋገጥ ማድረግ ፤

ወቅታዊ የምግብ፤ጤና እና ጤና ነክ ቁጥጥር ስርአት ተግባራዊ በማድረግ የምግብ፤የጤና እና ጤና ነክ አገልግሎት እና ምርት ተገቢነት እና አግባብነት ማረጋገጥ ፡፡

ህገ-ወጥ የምግብ ፤የጤና ነክ እና መድሃኒት ዝውውር በመቆጣጠር እና በመከላከል፤ የምርት ጥራት እና ህክምና መሳሪያዎች ደህንነት በመረጋገጥ፤ የህብረተሰቡን ጤና ማስጠበቅ ፡፡

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም አዲስ አበባ ደህንነቱንና ጥራቱ የተጠበቀ ምግብ ፤ጤናና ጤና ነክ ምርትና አገልጎሎት ከሚያገኙ አምስት የአፍሪካ ከተሞች አንዷ ሆና ማየት ፡፡

እሴቶች

  • ተጠያቂነት እና ግልጸኝነት
  • በእውቀት መመራት መስራት
  • ለሙያ ስነ-ምግባር ተገዥነት
  • ጥራትን ተቀዳሚ ተግባር ማድረግ
  • የህዝብ ጤና ማስቀደም
  • አድሎ አለመፈፀም
  • ውጤታማነት
  • ምላሽ ሰጪነት
  • አሳታፊነት
  • ህግ አክባሪነት
  • አርአያነት

የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባራት በአዋጅ 84/2016

  • የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከተቋቋሙ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተናጠል ተግባርና ኃላፊነት ተሰጥቶታል ፡፡
  • የምግቦችን ደህንነትና ጥራት ፤የመድሃኒቶችን ደህንነት ፤የፈዋሽነት ፤ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀም ፤የህክምና ባለሙያዎች ብቃትና አሰራር፤የኃይጅን፤ የአካባቢን ጤናን እና የጤና-ነክ ቁጥጥር የሚደረግበት ተቋማት የቁጥጥር ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ያረጋግጣል ፡፡
  • ለጤና ተቋማት፤ የመድሃኒት አከፋፋዮች እና ማከሚያዎች ፤የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል ፤ያድሳል ፤ያግዳል ፤ይሰርዛል፤
  • የጤና- ነክ ተቋመት የሙያ ፈቃድ ይሰጣል ፤የንጽህናና የጤና ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል ፡፡
  • የህፃናት ማቆያዎችን የሙያ ደረጃ ፈቃድ ይሰጣል ፤የንጽህና የጤንነትና ተስማሚነት ደረጃዎችን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል ፡፡
  • በምግብ፤ መድሃኒት፤የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ፤የጤና ባለሙያዎች እና የጤናና ጤና-ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማትን በሚመለከት የመረጃ መዕከል ሆኖ ያገለግላል ፡፡
  • በምግብ ወይም በመድሃኒት መመረዝ ወይም መበከል ምክንያት ለሚደርስ ሞት ፤የጤንነት መታወክ መንስኤ የሆነውን ንጥረ ነገር ልዩ ልዩ ናሙናዎችን በመውሰድ ምንነታቸው እንዲረጋገጥ ያደርጋል ፤ እርምጃ ይወስዳል ፡፡
  • አግባብ ባለው ህግ መሰረት የባህል መድሃኒት አዋቂዎች በባህል ህክምና ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ ይሰጣል ፤የባህል መድሃኒቱ ምን አይነት ይዘት እንዳለው በላብራቶሪ እንዲመረመር ያደርጋል ፤ያረጋግጣል፤ይቆጣጠራል ፡፡
  • በደረጃው የተፈቀደለት የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤ያድሳል፤ያግዳል ይሰርዛል ፤የባህል ህክምና ከዘመናዊ ህክምና ጎን ተጠናክሮ የሚሄድበት ስልት ይቀይሳል ፡፡
  • በባለስልጣኑ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማት ላይ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ምግቦች ፤መድሃኒቶችና ጥሬ እቃዎች በአግባቡ መወገዳቸውን ያረጋግጣል ፡፡
  • ህገ-ወጥ ምግቦችን ፤መድሃኒቶችና የጤና አገልግሎቶችን ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊ እርምጃዎችንም ይወስዳል ፡፡
  • አስተዳደሩ በሚቆጣጠርባቸው የጤና ተቋማት አበረታች መድሃኒቶች ፤የናርኮቲክ መድሃኒት፤ሳይኮትሮፒክ ንጥረ ነገሮች እና ፕሪከርሰር ኬሚካሎች ለህሙማን ማዘዝን ፤ማይልን ፤አጠቃቀምን ፤መመዝገብንና ሪፖርት ማድረግን ይከታተላል፡፡
  • በከተማው አስተዳደር ስር ያለ ጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማት ተገቢውን የሃይጅንና አካባቢ ጤና አገልግሎት መስፈርት ማሟላታቸውን ያረጋግጣል ፡፡
  • የስነ-ምግባር ግድፈት በሚያሳዩ የጤና ባለሙያዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ፡፡
  • ለስራው አስፈላጊ የሆኑትን የጥራት ምርመራ ላብራቶሪ ያደራጃል ፤ለሚሰጠው አገልግሎት አግባብ ባለው ህግ መሰረት ያስከፍላል ፡፡
  • የጤና ሙያ ስነ-ምግባር ጥሰትና የህክምና ስህተት በመፈፀሙ አቤቱታ ወይም ጥቆማ ሲቀርብ ይመረምራል ፤ እንደ አግባብነቱ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያድርጋል ፡፡
  • የጤና ሙያ ስነ-ምግባር ኮሚቴ አሰራር እና አደረጃጀት ደምብ አዘጋጅቶ ለከንቲባ ያቀርባል ፤ሲፀድቅ ስራ ላይ ያውላል ፡፡